እንጉዳይ የማምረት ሥራና ሊያስገኝ የሚችለው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ

አትራፊ የእንጉዳይን የማምረት ሥራ  ለገበያማቅረብና መሸጥን ጨምሮ ብዙ ካፒታልና ግዜን ይጠይቃል።

እንጉዳይን ለንግድ ለማምረት ላሰቡ ይህ ጽሁፍ ስለ፡

 •  እንጉዳይ ማምረት
 • ለገበያ ማቅረብና
 • የገበያ ውድድር

ማለፍ ይችሉ ዘንድ መሰረታዊ የመግቢያ ሀሳብ ይሆናቸዋል ብለን እናምናለን። እንጉዳይ የማምረት ስራ የጉለበትና  የግዜ መስዋዕትን በእጅጉ የሚጠይቅ ነው። እንጉዳይን የማምረት ስራን ለመጀመር ያሰበ ሰው ፡-

 • እንጉዳይን የማሳደግ ሂደት እጅግ ጥንቃቄና የቅርብ ክትትል የሚፈልግ መሆኑን መረዳት
 • ጠቀም ያለ ትርፍ ለማግኘት የሚያስቸሉ ተግባራትንና ግብዓቶችን መጠቀም ያለበት መሁኑንና
 • የተመሰረተ የገቢያ መስመር ለመዘርጋት ግዜውን ለመሰዋት መዘጋጀት አለበት።

በሀገራችን ያለው የእንጉዳይ ንግድ ሥራው በለበት ቦታዎች ሁሉ አንድ አይነት ገፅታ ያለው ሲሆን ይህም አምራቾች ምርታቸውን የአመራረት ሥልጠናና ግብዓት ለሚያቀርቡላቸው  ማዕከሎች መልሰው መሸጥ ሲሆን እነዚህም መዓከላት ራሳቸው ዋጋውን ወስነው ከደንበኞቻቸው የገዙትን እንጉዳይ ለተረካቢ ሆቴሎች፣ ሱፐር ማርኬቶችና ሬስቶራንቶች የሚሸጡበት ሁኔታ ነው ያለው። ይህም ሲሆን የእንጉዳይ አምራቾች ምርታቸውን ወደፈለጉበት ቦታ ሄደው ምርታቸውን የመሸጥ ነፃነቱ የላቸውም። በሌላም በኩል ይህን በመሰለው የእንጉዳይ ንግድ እያንዳንዱ የእንጉዳይ አምራች ከላይ ከተገለፁት ማዕከላት ጋር ለመወዳደርና (ገበያውን በአብዛኛው ስለተቆጣጠሩት)  ለምርቶቻቸው ገበያ በራሳቸው ለማግኘት ያዳግታቸዋል።

የእንጉዳይ አምራቾች ጥሩ ትርፍ ለማግኘት ምርታቸውን አከፋፋዮች ዘንድ ከመሸጥ ይልቅ በቀጥታ ለተጠቃሚዎች መሸጥ ይኖርባቸዋል።

ስለዚህ እንጉዳይን ለማምረት ያሰበና ምርቱንም ራሱ ለገበያ ማቅረብ ያሰበ ሰው በአካባቢ ያለን የእንጉዳይ ገበያወይንም በእንጉዳይ ማዕከላት ያልተያዘ የገበያ ክፍልን መጠቀም የመጀመሪያ ዓላማው መሆን አለበት።ገበያን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመያዝ የአነስተኛ ደረጃ እንጉዳይ አምራቾች ቀጣይ የሆነ   እንጉዳይ ምርት አቅራቢዎች መሆን ይኖርባቸዋል።

በእንጉዳይ የማምረት ስራ ትርፋማነት ቀጣይ የሆነ የእንጉዳይ ምርት ማምረትን ይጠይቃልና። ቀጣይ ያልሆነ  ምርት አምራች ቀጣይ የሆነ የምርት አቅርቦት መስጠት ያቅተዋል ። ቀጣይ ለሆነ የእንጉዳይ ማምረት ስራ ምርቱን  ገዝተው ከሚጠቀሙ ገዢዎች ጋረ ቀጣይ የሆነ ግንኙነት መፍጠር የግድ ነው። ለዚህም የተወሰነና የማይቀያየር  የምርት መጠን በተወሰነ የግዜ ክፍተት ውስጥ ለማቅረብ ከገዢዎች ጋር በመዋዋልና ይህንንም በትጋት  መተግበርን ይጠይቃል። የምርት ገዢዎች የምርት ፍላጎታቸውን ያለማሰለስ የሚያማላላቸውን አምራች ሁልግዜ      ምርጫቸው  ያደርጋሉ።

እንጉዳይን ማምረትለመጀመር ምን ያስፈልጋል?

እንጉዳይ የማምረት ስራ የእንጉዳይ ካልቸር ማግኘትና እሱንም ለረጅም ግዜ ጥራቱን ጠብቆ ማቆየት ችሎታ ያስፈልጋል።ይህንንም.ካልቸር ተጠቅሞ ማዘር ስፓውን ማዘጋጀት፣ ከዚያም ማሳደጊያ ሰብስትሬት የሚዘራበትን  ስፓውን ማዘጋጀት፣ መዝራትና እንጉዳይን ማሳደግ ሥራዎችን ያጠቃልላል። እንጉዳይ ማምረትን ስራ በዚህ ሂደት መጀመር ረጅሙ ሂደት ሲሆን አጭሩ ሂደት ደግሞ ለዘር የሚሆን ሰፓውን ከስፓውን አምራች ድርጅቶች ገዝቶ  በመጠቀም መጀመር ነው።

እንጉዳይን ማምረት ስራ ትርፋማነት

 ሁልግዜ በገበያ ሂደት ውስጥ የምርት ፍላጎት አምራቹ የሚያሳድገውን የእንጉዳይ አይነት፣ ምርጫና የምርት  መጠን ይወስናል። ኦይስተር ተብሎ የሚጠራው የእንጉዳይ ዝርያ በሀገራችን ጥሩ የሚባል የገበያ ፍላጎት ያለው ሲሆን፡ ጀማሪ አምራቾችም በዚህ ዝርያ እነዲጀምሩ ይመከራል። በተጨማሪም ኦይስተር ብዛት ባላቸው የግብርና ተረፈ  ምርቶች ላይ ማደግ መቻሉ በአነስተኛ ደረጃና መሀከለኛ በሆነ ወጪ ለማምረት ይቻላል። ከላይ እንደተገለጸው  የምርት መጠኑ በገበያ ሂደት ውስጥ ባለ የምርት ፍላጎት የሚወሰን ስለሆነ አምራቾች የምርት መጠናቸውን ከመወሰናቸው.አስቀድሞ ምርቱ በገበያ ያለውን ፍላጎትና ዋጋ ምርቱን ይገዛሉ ተብለው የሚገመቱ ገዢዎች ድረስ  በመሄድ ጥናት ማድረግ አለባቸው።

የእንጉዳይን የማምረት ስራ ለመጀመር የሚያስፈልጉት ወጪዎች፡

 • የመመስረቻ ወጪዎች (የቦታ/የቤት ኪራይ፣ መደርደሪያዎች፣ የመስሪያ ዕቃዎች)
 • የጥሬ ዕቃዎች /ግብዓቶች/ ወጪ (ዘር፣ ሰብስትሬት፣ የማሳደጊያ ዕቃ፣ የፓስቸራይዜሽን ወጪዎች፣ ምርታማነትን የሚጨምሩ የእንጉዳይ ማዳበሪያዎች)
 • የማምረት ሂደት ወጪዎች (የሰራተኛ፣ የውሀ፣ የእንጉዳይ በሽታዎችና ተባይ መከላከያ መድሀኒቶችና የማሳደጊያ ቤቶችንና የግቢን ንፅህና በጠበቂያ ግብዓቶች) እና
 • ጥቃቅን ወጪዎች ናቸው።

 ከእንጉዳይ ማምረት ስራ ትርፍ ለማገኘት በቀላሉ የማይታይ ግዜ ሊወስድ ይችላል። ይህም የሚሆነው ጀማሪ  አምራቾች በአብዛኛው ይፈጠራሉ ብለው የማይጠበቁዋቸው ችግሮች ለምሳሌ የቀጨጨ የእንጉዳይ ዕድገት፡ ተባይና የገበያ አለመረጋጋት ወይንም ተለዋዋጭ የምርት ዋጋ በገበያ ስለያያጋጥሟቸው ስለሚችል ነው ነው። አንድ የእንጉዳይ አምራች ከሥራው ትርፋማነትን ለመጎናፀፍ የሚከተሉትን ነጥቦች በደንብ ሊረዳ ይገባዋል።

 •        ከማምረት ሥራው ለማግኘት የታቀደውን  የገቢ / የትርፍ መጠንን ለሚያመጣ የሚያስችል          ግብዓቶች ማዘጋጀት መቻልን ማረጋገጥ
 •        እንጉዳይን ለማሳደግ የሚጠቀመው ሰብስትሬት ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ መሆኑን ማረጋገጥ
 •        የሚጠቀመው የእንጉዳይ ዘር ጥራት ማረጋገጥ
 •        የተወሰነ ክብደት ላለው ለመዘራት በተዘጋጀ እርጥብ ሰብሰትሬት የሚጠቀመው የዘር መጠን          ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ
 •        ለእንጉዳይ እድገት የሚያስፈልጉ የብርሃን፣ የሙቀት፣ የኦክስጅንና የአየር እርጥበት መጠን              በትክክል መሟላታቸውን ማረጋገጥ
 •        የእንጉዳይ እድገት ሂደት በባክቴሪያ፣ በቫይረስ፣ በተቀናቃኝ ሞልዶችና በተባዮች                           አለመጠቃታቸውን ማረጋገጥ
 •        የእንጉዳይ ምርት መመረት ባለበት በትክክለኛው ግዜ መመረቱን ማረጋገጥ

 ለምሳሌ ያህል ለላይ ከተዘረዘሩት ነጥቦች ውስጥ ሁለተኛውን ብንመለከት ለኦይስተር ማሳደጊያነት በብዛት ጥቅም ላይ የሚውለው የጥጥ ፍሬ ገለባ እስከ 150% ምርት የመስጠት ብቃት (ባዮሎጂካል ኢፊሸንሲ) አለው። ይህም ማለት ከ 1 ኪሎግራም የጥጥ ፍሬ ገለባ 1.5 ኪሎግራም ትኩስ የእንጉዳይ ምርት ማግኘት እንችላለን ማለት ነወ።

ከዚህም በመነሳት አሁን ባለው ዋጋ መሰረት የእንጉዳይ ማሳደጊያ ዕቃዎች የሚያቀርቡ ማዕከላት የአንድ ኪት ዋጋ ከ30-45 ብር የሚደርስ ሲሆን ይህም ኪት 2 ኪሎግራም የጥጥ ፍሬ ገለባ ና 1% የዘር መጠን ይይዛል። ከላይ በተገለፀ ው ምርት የመስጠት ብቃት (ባዮሎጂካል ኢፊሸንሲ) መሰረት ከአንድ ኪት የምናገኘው ምርት 3 ኪሎ ግራም ይሆናል ማለት ነው።  ነገር ግን ይህ የምርት መጠን ከአንድ ኪት ሲገኝ አይታይም። ለዚህም ብዙ ምክኒያቶችን መጥቀስ ቢቻልም መሰረታዊው ምክኒያት ግን የዘር መጠን ማነስ ችግር ነው። (ስለ ዘር መጠን ተጨማሪ ንባብ)

ከላይ እንደተጠቀሰው የጥጥ ፍሬ ገለባ የምርት የመስጠት ብቃት የሚያወርዱ ብዙ ምክኒያቶች እንዳሉ ሁሉ  አንዲሁም ይህን ብቃት ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ ግብዓቶች መኖራቸውን በገንዘብ ያሻል።

የዕንጉዳይ ሰላጣ አዘገጃጀት

ኦይስተር  ለመብላት ደስ የሚል የምግብ ፍላጎትን የሚያነሳሳ የእንጉዳየ አይነት ነው። ነገር ግን አዘገጃጀቱ የጣዕሙን መመቸትና አለመመቸት በእጅጉ ይወስነዋል።  ኦይስተር በሰላጣ መልክ ተዘጋጅቶ በትኩስነቱ ቢቀርብ የኦይስተርን መልካም ጣዕም ማጣጣም ይቻላል።

ግብአቶች

 • ¼ስኒ ነጭ ከወይን የተሰራ ቪኒገር
 • 2 የቤይ ቅጠሎች
 • ጨው (በጣቶች መሀከል በሚያዝ መጠን)
 • ኦይስተር እንጉዳይ 800 ግራም (ግንዱ የተወገደና  በቢላ የተሰነጠቀ)
 • 6 ማንኪያ ኢክስትራ ቨርጂን የወይራ ዘይት
 • 1 መያልተላጠ ሎሚ። ልጣጩ ይፈጫል፡ ጭማቂው ለኃላ አገልግሎት ይቀመጣል።
 • 1 ወይንም ሁለት የደረቁ ቃሪያዎች። ፍሬያቸው ይወገድና ይከተፋሉ።
 • 3 ማንኪያ የተከተፈ የፐርስሊ ቅጠል
 • 3 ራስ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት
 • 4 የተከተፈ የዓሳ ፊሌቶOyster salad 

አዘገጃጀት            

 1. 3 ማንኪያ ዉሃ በመጥበሻ ውስጥ ይጨምሩ። ከዚያም  ነጭ የወይን ቪኒገር፣ የቤይ ቅጠሎችና ጨው የጨምሩና ያፍሉት።
 2. ውሀው ሲፈላ እንጉዳዩን ይጨምሩና ለ8 ደቂቃ ይቀቅሉት። ከዚያም ዉሃውን ያጠንፍፉት (ትንሽ ፈሳሽ ቢመስልምየእንጉዳዩን መጠን እንዲቀንሰው ያደርጋል።)
 3. ሌላ መጥበሻ አዘጋጅተው የወይራ ዘይት፣ የተፈጨ የሎሚ ልጣጭ፣ ቃሪያ፣ ፐርስሊ፣ ነጭ ሽንኩርትና የዓሳ ፊሌቶቹን  ይጨምሩና መጥበስ ይጀምሩ።
 4. ዘይቱ ሲግል ቀድሞ የተዘጋጀውን እንጉዳይ በመጨመር እያማሰሉ ከ5-6 ደቂቃዎችያህል መጥበስ።
 5. በመጨረሻም የሎሚ ጭማቂውን መጨመርና ከእሳት ላይ ማንሳት። ከዚያም በኃላ ጣዕሙን ቀምሰው ሳይበርድ ሞቅ እንዳለ ማቅረብ።

 

 

የእንጉዳይን ምርታማነት  የሚያሳድጉ ተግባራትና ግብዓቶችና

Pleurotus ostreatus

በአሁኑ ግዜ የኦይስተር እንጉዳይ አምራቾች አየበዙ ያለበት ሁኔታ ነው። ኦይስተር ከሌሎች የእንጉዳይ ዓይነቶች አንጻር አመራረቱ ቀላል ቢሆንም ብዙውን ግዜ እንደሚሰማውና እንደሚታየው ግን ብዙ አምራቾች የጠበቁትን ያህል ከማምረት ሥራው ተጠቃሚዎች አይደሉም። ይህም ሊከሰት የሚችልባቸው ምክኒያቶች ዋናው ለእንጉዳይ እድገት በተለይም ለፍሩት ቦዲ እድገት አስፈላጊ የሆኑትን መሰረታዊ የከባቢ ሁኔታዎችን (የሙቀት መጠን፣ የአየር ዕርጥበት መጠን፣ የኦክስጅን መጠን፣ የብርሀን መጠን) ያለሟሟላት ችግር ነው። በዚህም ምክኒያት ጥቂት የማይባሉ የእንጉዳይ አምራቾች ምርታቸውን ሊያጡ የቻሉበት ክስተቶች እንዳለ ግልፅ ነው። ይህም ችግር ከፍተኛ የምርት ዕጦቶትን የሚያስከትል በተለይም ከወቅቶች መቀያየር ተከትሎ የሚከሰተውን ተፈጥሮአዊ የሙቀት መጠንና የአየር ዕርጥበት መጠን መቀያየር (መጨመር ወይንም መቀነስ) አንፃር  አምራቾች ማድረግ ያለባቸውን የእንክብካቤ ለውጥ ማድረግ ሳይችሉ ሲቀሩ ነው።

ከላይ የተገለፀውመሰረታዊ የከባቢ ሁኔታዎችን ማሟላት ምርታማነትን ከመጨመር ረገድ አንዱና ዋነኛው ሲሆን ትክክለኛ የዘር መጠንና የተጨማሪ ንጥረ-ነገር ለጋሽ ማዳበሪያዎችን መጠቀም ምርታማነትን በእጅጉ የማሳደግ ግልጋሎት አላቸው። ይህም ሲሆን በእንጉዳይ በሽታዎችና ተባዮች የሚከሰተውን የምርት ውድመትን መከላከልን ጨምሮ  በእንጉዳይ የማምረት ሥራ ውሶጥ እንደ ዋና ሥራተደርገው መወሰድ እንዳለባቸው መገንዘብ ያሻል።

ከዚህ በታች ያለው ፅሁፍ የእንጉዳይ የዘር መጠንና የንጥረ-ነገር ለጋሽ ግብዓቶች በምርታማነት ላይ ያለቸውን ሚና ይዳስሳል። በመጨረሻም በተባዮች፣በተቀናቃኝና በሽታ አምጪ ፈንገሶች፣ባክቴሪያዎችና ቫይረሶች ሊያደርሱ የሚችሉት የምርተ ውድመት ትኩረት ሊሰጠባቸው የሚገባ እንደሆነ ለማስገንዘብ ቀርቦአል።

1. የስፓውን/ የዘር/ መጠን

የዘር መጠን የሚለካው ለመዘራት ከተዘጋጀው ከእርጥብ ሰብስትሬት አኳያ በፐርሰንት የሚለካ ነው። የዚህ ልኬት መጀመር ምክኒያት የዘር መጠን የእንጉዳይን ማምረት ሂደት ላይ አሉታዊና  አዎንታዊ ተፅእኖዎችን ያዳድራል። የዘር ትክክለኛ መጠን (በፐርሰንት) ለመወሰን ግዜ፣ ከምርታማነትና ከኢኮኖሚ ረገድ የሚሰራ የጥቀምና-የጉዳት ትንተና ያስፈልጋል። የእንጉዳይ ዘር መጠን በእንጉዳይ በማምረት ሂደት ላይ ያለውን ተፈጥሮአዊ ተፅዕኖዎች የተረዳ ማንኛውም የእንጉዳይ አምራች ከላይ የተጠቀሰውን የጥቀምና-የጉዳት ትንተና  ከራሱ አኳያ ሰርቶ መጠቀም ያለበትን የዘር መጠን መወሰን ይችላል።

ብዙ የምርምር ውጤቶች እንደሚያመለክቱት አማካይ የዘር መጠን ከ3-5% ነው። ይህም የዘር መጠን ልከ ውሳኔ በአብዛኛው የዘር መጠን ከምርታማነት ረገድ ያለውን ተፅዕኖ ብቻ ያማከለ ነው። ስለዚህም በሃገራችን ያሉ ብዙ የእንጉዳይ አምራቾች የሚጠቀሙት የዘር መጠን ከላይ ከተጠቀሰው በጣም ያነሰ ነው (1%)። ይህም የሆነበት ምክኒያት የዘር ዋጋ ውድ ስለሆነ ነው።

ብዙ ጥናቶችና ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት 5% የዘር መጠን 1%ን ተጠቅመን ከምናገኘው የእንጉዳይ ምርት በ50% ያህል ይጨምራል። 2.5% የዘር መጠን 1% ተጠቅመን ከምናገኘው የእንጉዳይ ምርት በ16% ያህል ይጨምራል።

የዘር መጠን ማነስ በእንጉዳይ ማምረት ሂደትና ምርታማነት ላይ ያለው አሉታዊ ተፅዕኖ በሁለት መንገድ ይገለጣል።

ሀ. የሻጋታ ጠቀላላውን ሰብስትሬት የሚሸፍንበትን ግዜ ያራዝማል በዚያውም የምርት መሰብሰቢያ ግዜንም እንዲሁ።

ለ. በሻጋታ ያልተሸፈነ ሰብስትሬት (ከላይ በተጠቀሰው የግዜ መራዘም ምክኒያት) በባክቴሪያና በፈንገስ በመበስበስ (በመበላት) እንጉዳይ ከሰብስትሬቱ ማግኘት የሚገባውን ንጥረ-ነገር በማሳጣት ምርታማነትን ይቀንሳል። ፓስቸራይዝ የተደረገ ሰብስትሬት ስተራላይዝድ ከተደረገ ሰብስትሬት ይልቅ ብዙ ዘር ይፈልጋል ምክኒያቱም ስተራላይዝድ የተደረገ ሰብስትሬትባሽና ከሌሎች ጎጂ ህዋሳት ነፃ ስለሆነ የሻጋታ እድገት ግዜ መራዘም ምንም ተፅዕኖ ስለማያመጣ ነው። በተጨማሪም ፓስቸራይዝ በተደረገ ሰብስትሬት የሻጋታ እድገት የሚከናወንበት ቤት የሙቀት መጠን ለሻጋታ እድገት ተመራጭ ከሆነው ከ250C  ወደ 15-200C  ዝቅ ማድረግ በባክቴሪያና በፈንገስ የሚደርሰውን መበስበስ መከላክል ያስችላል።

2. አዝጋሚ የንጥረ-ነገር ለጋሽ ማዳበሪያ

ለዕንጉዳይ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚጠቅሙ ብዙ ንጥረ -ነገሮች ቢኖሩም እነዚህን በቀላሉ መጠቀም  ግን አዳጋች ነው። ይህ የሆነበተ ምክኒያት የምንጠቀመው ንጥረ-ነገር ለጋሽ ማዳበሪያ የምናሳድገውን እንጉዳይ ከማፋፋት ይልቅ ሌሎች በሽታ አምጪ ተዋሲያንንና ተቀናቃኝ ፈንገሶችን እድገት በማፋጠን ጭራሹን ምርት እንዳናገኝ የሚያደርግበት ሁኔታ/አጋጣሚ የላቀ በመሆኑ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ንጥረ-ነገር ለጋሽ ማዳበሪያ የተደረገለት እንጉዳይ ማሳደጊያ ሰብስትሬት ካልተደረገለት ይልቅ የተለየ እንክብካቤ ያስፈልገዋል።

ለእንጉዳይ ምርታማነት መጨመር የሚውሉ ብዙ አይነት ግብዓቶች ሲኖሩ በተለምዶ ከማሳደጊያ ሰብስትሬት ጋር ተመጥነው የሚጨመሩ እንደ የስንዴ ፉርሽካ የመሳሰሉትንም ይጨምራል። የስንዴ ፉርሽካን ለማዳበሪያነት ለመጠቀም ዋና ሰብስትሬቱና ፉርሽካው በሚፈለገው መጠን (አብዛኛውን ግዜ 10-15%) ከተደባለቁ በሗላ አብረው ስተራላይዝድ መደረግ አለባቸው። ይህ ዘዴ በፓስቸራይዜሽን ስለማይሰራና ስተራላይዝ ማድረጊያ ማሽን ስለሚያስፈልገው ከፍተኛ ወጪን ይጠይቃል።

አሁን አሁን አዳዲስ የምርምር ውጤት የሆኑ ወጤታማነታቸው የተረጋገጠና ለአጠቃቀም ምቹና ቀላል እንዲሁም ፓስቸራይዝድ በተደረገ ሰብስተሬት ላይ መጨመር የሚችሉ የእንጉዳይን ምርታማነት የሚጨምሩ ማዳበረያዎች በገበያ ይገኛሉ። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ አዝጋሚ የንጥረ-ነገር ለጋሽ ማዻበሪያ የሚባለው ሲሆን ይህም የደረቅ ሰብስትሬት ክብደትን  ከ3-6% ያህል ይጨመራል። ብዙ ተሞክሮ ያላቸው የእንጉዳይ አምራቾች እንደሚናገሩት የ 6% ማዳበሪያ በማሳደጊያ ሰብስትሬት ላይ መጨመር የኦይስተር እንጉዳይን ምርታማነት እስከ 90% ያህል ከፍ የማድረግ ችሎታ ይኖረዋል (የሚከተለውን ግራፍ ይመልከቱ)። ከዚህም በተጨማሪ የአዝጋሚ የንጥረ-ነገር ለጋሽ ማዻበሪያ ን መጠቀም የምርት ግዜን እስከ 3 ቀን ያህል ያሳጥራል። 

ይህንን ማዳበሪያ ለመጠቀም የሚያስቡ የእንጉዳይ አምራቾች አንድሊያስተውሉት የሚገባ ሁኔታ አለ። ይህም ማዳበሪያ የተደረገበት የእንጉዳይ ማሳደጊያ ሰብስትሬት ከሌላው የተለየ ከፍተኛ ሙቀት ይኖረዋል። የሙቀት መጨመር መጠንም ከተጠቀምነው የሰብስትሬት መጠን ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት አለው። ይህ ከፍተኛ ሙቀት ዝም ከተባለ ሻጋታን እድገት ለገታ ስለሚችል ይንን ማዳበሪያ የሚጠቀሙ አምራቾች ይህን የሰብስትሬት ከፍተኛ ሙቀት የሚከላከሉበት መንገድ ሊኖራቸው ይገባል። ይህም የሰብስትሬቱንና እንዲሁም የጨለማ ቤትን የአየር ሙቀት ዝቅ ማድረጊያ መንገዶችን መፈለግ ይኖርባቸዋል። 

 1. በሽታ አምጪህዋሳትን፣ ተቀናቃኝ ፈንገሶችንና ተባዮችን መከላከልና መቆጣጠር

የእንጉዳይን ሞርታማነት የሚቀንሱ ችግሮችን መቅረፍ በራሱ ምርታማነትን መጨመርና ከሥራውም የምናገኘውን ትርፍ ማስጠበቅ እንደሆነ ለሁሉም ግልፅ ነው። የእንጉዳይን ምርታማነት የሚቀንሱ ችግሮች በባክቴሪያና በቫይረስ የሚከሰቱ በሽታዎች፣ ይንጉዳይን ምግብን የሚሻሙ ተቀናቃኝ ፈንገሶችና ሻጋታንና የእንጉዳይን ፍሩት ቦዲ በመብላት የሚጉዱ ተባዮች ናቸው። 

ሰንጠረዥ 1. የሚከተለው ሰንጠረዥ የእንጉዳይን እድገት ከሚያደናቅፉና ምርታማነትን የሚያሳንሱ ዋና ዋና የእንጉዳይ በሽታ አምጪ ህዋሳትና ተባዮችን ይገልፃል።

ምድብ የበሽታ/የጉዳት መንስኤ የሚያጠቃው  እድገት ደረጃ የሚያስከትለው ጉዳት የሚያስከትለው የምርት ውድመት
ሞሉስክ ስለግ (Slug) ፍሩት ቦዲ በማደግ ላይ ያሉ  ፍሩት ቦዲዎችን በመመገብ
አርትሮፖድስ ምስጥ ሻጛታ የሻጛታን ዋና ምግብ የሆነውን ሴሉሎስን በመመገብ 80-90%
ሸረሪት ፍሩት ቦዲ በማደግ ላይ ያሉ  ፍሩት ቦዲዎችን በመመገብ
ፈንገስ ናት ላርቫ (fungus gnat larva) ሻጋታንና ፍሩት ቦዲ በማደግ ላይ ያሉ  ፍሩት ቦዲዎችንና ሻጋታን  በመመገብ 60-100%
ፈንገስ ተቀናቃኝ ሞልድ የፍሩት ቦዲና የሻጋታ ዕደገትን ምግንን በመሻማትና ተእንጉዳይን እንገት የሚገቱ ኬሚካሎችን ማመበጨት 70%
በፈንገስ የሚከሰቱ በሽታዎች ሻጋታንና ፍሩት ቦዲ የፍሩት ቦዲ በቀላሉ መሰባበር፣ ቀለም መቀየርና ማበስበስ 70%
ባክቴሪያ ብራውን ስፖት (Pseudomonas strutzeri) ፍሩት ቦዲ የፍሩት ቦዲ በቀላሉ መሰባበር፣ ቀለም መቀየርና ማበስበስ 27-37%
የሎው ብሎች (Pseudomonas agarici) ፍሩት ቦዲ የፍሩት ቦዲ መጨጭና በቀላሉ መሰባበር፣ መጥፎ ሽታ በሽተት
ባክቴሪያል ብሎች (Pseudomonas alcaligens) ፍሩት ቦዲ የፍሩት ቦዲ በቀላሉ መሰባበር፣ ቀለም መቀየርና ማበስበስ 27-37%

ከላይ እንደተገለፀው በባክቴሪያና በቫይረስ በሚከሰቱ በሽታዎችና በተባዮች በኦይስተር እንጉዳይ እድገትና ምርታማነት ላይ ብዙ ጉዳት ያደርሳሉ። እንደ የሎው ብሎች፡ ባክቴሪያል ሮትና ብራውን ስፖት ከ 27-37% በላይ የሆነ የምርት ውድመት የሚያስከትሉ በባክቴሪያ የሚከሰቱ በሽታዎች ናቸው። ተቀናቃኝ ሞልዶችና በሸታ አምጪ ፈንገሶች የኦይስተር አንጉዳይን ምርት  እስከ 70% ሊያሳጡ የሚችሉና ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በእጅጉ የሚያስቀሩ ችግሮች ናቸው።

በሌላ በኩል ደግሞ የኦይስተር እንጉዳይ እርሻ ላይ የሚከሰቱ ተባዮች ሲሆኑ እነዚህም እንደ ጥቃት መጠኑ ሁኔታ ምርታማነትን እስከማሳጣት የሚያደርሱ ናቸው። ከእነዚህም መሀከል እንደ ፈንገስ ናት ላርቫ(Fungus gnat)፣ ስለግ፣ ምስጥ፤ ሸረሪትና ሌሎች የበራሪ ነፍሳት ላርቫ ዋናዋናዎቹ ናቸው።

 

Spawns! Big Discount!

HIGH-YIELDING, SUPERIOR QUALITY

MUSHROOM SPAWNS

The Elixir spawn laboratory, the sister Enterprise of Elixir Mushroom is glad to announce that it has made available,  HIGH yielding spawns of shiitake and Oyster strains for sale.

Order Now!

We receive Customers’ Orders from EVERY PART OF THE COUNTRY, & Send our products to customers where they are, with the best transport medium available. CUSTOMERS NOT NECESSARILY SHOULD APPEAR IN PERSON.

Our packaging method ensures full protection against product damage that might occur during long distance transport. 

See our products page

 

Oyster Mushroom Morney

Morney1
Ingredients
• 4 cups coarsely chopped oyster Mushroom
• 2 large cloves garlic, minced
• 4 tablespoon butter
• ½ pound shrimp, shelled and deveined
• 1 cup fresh pea pods, halved
• 2 tablespoon four
• 2 cup chicken broth
• 1 cup heavy cream
• ¼ cup dry white wine
Cooked and buttered pasta
freshly ground black pepper
Grated parmesan cheese

Saute’ mushroom and garlic in 2 tablespoon butter for 3 minutes. Add shrimp and pea pods; simmer until shrimp are pink. In separate pan, melt remaining butter and whisk in flour. Cook over low heat for 3 minutes. Slowly whisk in broth. Add cream and wine; heat without boiling, stirring constantly until thickened. Mix creak sauce with cooked pasta, and stir in mushroom mixture. Season to taste with salt and pepper. Heat through; serve sprinkled with Parmesan cheese.

Oriental Oyster Mushroom and Steak

oriental

Ingredients
• 1 teaspoon grated ginger root
• cup soy sauce
¼ cup cooking sherry
• 6 table spoon vegetable oil
• 4 cloves garlic, crushed
• 2 brown sugar
• 1 pound flank steak, cut into 2-inch stripes
• 3 green onions, chopped
• ½ cup chopped onion
• 1 cup chopped green pepper
• 3 cups coarsely chopped oyster Mushrooms
• 2 teaspoon cornstarch dissolved in 1 teaspoon water
Hot cooked rice to serve with
Procedure
Combine ginger, soys sauce, sherry, 2 table spoon oil, garlic, and sugar in non-metalic bowl. Marinate beef stripes in this mixture unrefrigerated for 3 hours or refrigerated for 4 to 12 hours (add ¼ cup water to marinade if needed). Saute’ onions and pepper in 2 table spoon oil until tender-crisp. Add mushrooms and cook 3 minutes more on medium-high heat, stirriing constantly. Remove to plate. Stir-fry beef stripes in remaining 2 tablespoons oil over high heat for about 3 minutes. Add marinade and birng to boil. Add dissolved cornstarch, mixing constantly, until clear and thickened. All vegetable and mushroom mixture. Bring to boil until heated though. Serve over rice.

የአንጉዳይን ዘር /ስፓውን/ አቅርቦት

ብዙዎች እንጉዳይን ለማምረት ቢፈልጉም የአንጉዳይን ዘር /ስፓውን/ አቅርቦት ውስን በመሆኑና፤ በእንጉዳይ ንግድ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ለአሰለጠኑዋአው ደንበኞቻቸው ብቻ ስለሚሸጡ ወይንም ስለሚያስቀድሙ የእንጉዳይን ዘር ማግኘት ከባድ አድርጎታል። የእንጉዳይን ዘር ማምረት በመስኩ የሚፈለገው እውቀትና የማይሲሊያ ባህሪን በመረዳት ምርታማ የሆነንና ያልሆነን ማይሲሊያ የመለየት ልምድ ማካበትን የጠይቃል። አንዲሁም ምርታማም የሆነ የእንጉዳይ ዘር አይነት /ስትሬይን/ ብዙ ግዜ ሲባዛ ስለሚያረጅ የሚሰጠው ውጤትም ውስን ይሆናል። ይህንንም አጢኖ የዘሩን አይነት /ስትሬይን/ በወቅቱ መቀየር እያደገ ላለው የመሽሩም ኢንዱስትሪ ትልቅ አስተዋጽዖ አንደሚኖረው አያጠራጥርም።

ኢሊክሰር መሽሩምስ! በእንጉዳይ ዘር ምርምርና በኦይስተር መሽሩም ዘር አቅርቦት ላይ እየሰራ ይገኛል። በእንጉዳይ ዘር ምርምሩም በአዳዲስ የኦይስተር ስትሬይን ዘሮችን ማዘጋጀት ከመቻሉም በተጨማሪ በአገለገሉ ጠርሙሶች በቻ ተወስኖ የነበረውን የዘር ምርት በፕላስቲክ ባግ በመቀየር የዘር አቅርቦትንና የዘር ዋጋን በእጅጉ አሻሽሏል። ከዚህም የተነሳ በሐዋሳ ብቻ ተወስኖ የነበረውን አገልግሎቱን አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ክልል ከተሞች አያዳረሰ ይገኛል። የዘር ምርቶቻችንም በባለ 250 ግራም፤ 500 ግራምና ባለ 1 . . ፕላስቲክ ባግ ተዘጋጅተዋል። ዋጋችንም የህበረተሰባቸንን አቅም ያማከለ ነው።

የኦይስተር እንጉዳይ ዘር ከፈለጉ መጠኑናና የዕሽግ ክበደቱን ጠቀሰው በሚቀጥለው አድራሻ የጠይቁን! ፈጣን ምላሽ አንሰጥዎታለን። 

ስልክ:    09 21 45 28 26  ኢሜይል: elixirmushrooms@gmail.com 

For updated information about our products click here